"Gafat Endowment is a people to people non-governmental development organization committed to generate income from investing endowments on strategic industries/ services mainly in the areas of agriculture, mining, water resources, education and health; and bestow part of the money earned from the investment back to the people to help transform the region and improve the livelihood of the people of Amhara national regional state in a sustainable manner".

Gafat Endowment operates with credibility & dedicated to institutional excellence.

Gafat Companies

Design by Za Studio
   

Find Us  

   

News  

   

 

የጋፋት ኢንዶዉመንት አንዱ ኩባንያ የሆነዉ ጣና ፍሎራ ከ አበባዉ ምርት በተጨማሪ የተለያዩ ለሀገር ዉስጥ እና ለዉጭ የሚሆን አቮካዶ አሁን ምርት ወደመስጠት ደርሷል፡፡In addition to the flower production, Tana Flora is also available for domestic and international use Avocados are now in production

 

27/2021 

የጋፋት ኢንዶውመንት እ.ኤ.አ የ2020 የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2021 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ዛሬ በ 27/2021 የሁሉም ኩባንያ ሀላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ቀርቧል::

May be an image of one or more people, people standing, people sitting and indoor

May be an image of 4 people, people standing, people sitting and indoor

 

የስልጠና ዜና(13/05/2013-15/05/3013)

በጋፋት ኢነዶዉመንት አስተባባሪነት የኢንዶዉመንቱ እና የሁሉም ኮባንያዎች የማኔጅመንት ሰራተኞችን እና ሀላፊዎችን

ያካተተ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት በሚል ርእስ፡-
§ አቶ ጸጋየ ለገሰ ከአሜሪካ በአካል በመገኘት
§ አቶ ይሰሃቅ ሻታ ከአሜሪካ ዙም ሚቲንግ በመጠቀም እንዲሁም አቶ የሱስ ወርቀ ዛፉ ከ አድስ አበባ የማነቃቂያ ንግግር በማድረግ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በባህርዳር ስራ አመራር አካዳሚ አዳራሽ ተሰጥቷል፡፡
 
ምስሉ ሊይዝ የሚችለው:- አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች እና የተቀመጡ ሰዎች
 
 
ምስሉ ሊይዝ የሚችለው:- አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች እና ቤት ውስጥ

29/08/2011ዓ.ም

ኢንዶውመንቱ በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት የአፈጻጸም ውስንነት መንስኤዎችን ለይቶ በመፍታት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ጋፋት ኢንዶውመንት እ.ኤ.አ የ2019 በጀት አመት አንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ፡፡በግምገማውም ኢንዶውመንቱ በአራቱ የትኩረት መስኮች ለማከናወን ያቀዳቸው ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

በዚህም ከኢንቨስትመንት አንጻር በበጀት አመቱ ለማከናወን የታቀደው ባህር ዳር የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ ፋብሪካን ማቋቋም ሲሆን ይህን እውን ለማድረግም በሩብ አመቱ የተከናወኑት ተግባራት በቀጣይ ፋብሪካውን ለማቋቋም መሰረት የጣሉ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

በማህበራዊ ልማት ዘርፍ ከዚህ ቀደም ኢንዶውመንቱ ያከናወናቸውን የማህበራዊ ልማት ስራዎችን ውጤታማነት መከታተልን ጨምሮ በበጀት አመቱ ለመገንባት የታቀደውን ትምህርት ቤት ለመገንባት የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በጥንካሬ ተቀምጠዋል፡፡

በአቅም ግንባታው ዘርፍም የሰው ኃይሉን በአመለካከትና በክህሎት ለማብቃት የተከናወኑ ጅምር ተግባራትም እንዲሁ፡፡

የፋይናንስ አቅምን ከማሳደግ አንጻርም ምንም እንኳ በሚፈለገው ልክ ባይሆንም ጅምር ውጤቶች መኖራቸውም ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢንዶውመንቱ በሩብ አመቱ ለማከናወን ካቀደው አንጻር አፈጻጸሙ በቀጣይ እያንዳንዱን ተግባራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመላካች ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ የለውጥ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ተግባራትን በእነዚህ መፈፀም፣የሰው ኃይሉን አጠቃላይ ቁመና ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ለማድረስ የአቅም ክፍተቶችን ከወዲሁ መለየትና ይህን ሊቀርፉ የሚችሉ ስልጠናዎችን መስጠት፣የበጎ አድራጎት እና የማህበራዊ ልማት ስራዎችን በወቅቱ በመፈፀም ህብረተሰቡን ከዚህ ቀደሙ በበለጠ ተጠቃሚ ማድረግ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ በግምገማ መድረኩ ተገልጿ፡፡

ከዚህ ባሻገር የባህር ዳር የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ጋር ተያይዞ የተጀመሩ ስራዎችን ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን ዳር ማድረስ እና በየኩባንያዎቹ በበጀት አመቱ ለማከናወን የታቀዱ የማስፋፊያ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ተግባር በመቀየር የኩባንያዎችን አቅም ይበልጥ በማሳደግ ለኢንዶውመንቱ አላማ ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገውን ሃብት የማመንጨት ተግባራቸውን በብቃት እንዲወጡ ማስቻልም እንዲሁ፡፡

 

 

04/05/2011ዓ.ም

ኢንዶውመንቱ የማህበራዊ ልማት ተግባሩን በአዲስ መልክ በመቃኘት ከዚህ ቀደሙ በበለጠ በዘርፉ ሊሰማራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ዘርፉንም ከስራ እድል ፈጠራ ወደ ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ እንዲያዞርም ተጠቁሟል፡፡

የጋፋት ኢንዶውመንት ቦርድ ቅዳሜ ጥር 2/2011 ዓ.ም ስብሰባውን አካሄደ፡፡በስብሰባው የኢንዶውመንቱን እ.ኤ.አ የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ገምግሟል፡፡በግምገማውም በጥቅሉ የኢንዶውመንቱ የበጀት አመቱ አፈጻጸም የተሻለ መሆኑንን አመላክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በግምገማው በኢንዶውመንቱ ኩባንያዎች መካከል ያለው የአፈጻጸም ልዩነት በድክመት ተቀምጧል፡፡ የማህበራዊ ልማት ዘርፉም የሚጠበቀውን የመጨረሻ ግብ ከማሳካት አንጻር ውስንነቶች መስተዋላቸውም እንዲሁ፡፡እነዚህንና ሌሎች በበጀት አመቱ የተስተዋሉ እጥረቶችን መነሻ በማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አመላክቷል፡፡

በዚህም የማህበራዊ ልማት ተግባራቱን በማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ላይ ማተኮር፣አማራጭ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እየለዩ መሰማራት፣በኩባንያዎችን አፈጻጸም ረገድ የሚስተዋለውን ልዩነት በማሻሻል ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ማምጣት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡በተጨማሪ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ዘርፍ ለመሰማረት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ወደ ተጨባጭ ምዕራፍ ሊያሸጋግሩ የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በመጠቆም ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ቦርዱ የውጪ ኦዲተር ሪፖርትን አድምጦ ያጸደቀ ሲሆን የኢንዶውመንቱን እ.ኤ.አ የ2019 በጀት አመት እቅድንም ገምግሟል፡፡ በዚህም ከእቅዱ አንጻር መስተካከል የሚገባቸውን ነጥቦች በመጠቆም ባህር ዳር የግብርና ምርቶች ማቀነባበርያ ፋብሪካን የማቋቋሙ ተግባር ተጨማሪ ጥናት ተካሂዶበት በትኩረት እንዲሰራ በማለት እቅዱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡  

1/4/2011

የጋፋት ኢንዶውመንት ኩባንያ የሆነው ላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ከአጋር አካላት፣ደንበኞችና ተቋራጮች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የውይይት መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ  መልዕክት የከፈቱት የጋፋት ኢንዶውመንት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ በላቸው የውይይቱን አላማ አስመልክቶ እንደተናገሩት ኩባንያው በተሰማራበት የጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት ለክልሉ ልማት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም የባለ ድርሻ አካላት፣የደንበኞችና ተቋራጮች አስተያየት ሚና ከፍተኛ መሆኑንም እንዲሁ፡፡

በውይይቱ የመወያያ ጽሁፍ በላሊበላ የጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ስራ አስኪያጅ በአቶ ፍሰኃ ወንድይፍራው የቀረበ ሲሆን በዚህም ኩባንያው ከተቋቋመ ጀምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራትና ያጋጠሙት ችግሮች ቀርበዋል፡፡ከዚህ ባሻገር የአገልግሎት ጥራት፣ተደራሽነት፣ስነ ምግባርና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚሉት የመወያያ ሃሳቦች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በዚህም ኩባንያው ለእነዚህና መሰል ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ከመሆኑ ባሻገር የእውቀትና ክህሎት ደረጃቸው ከፈ ያለ  ባለሙያዎች ባለቤት ብሎም በስነ ምግባር ዙሪያ በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚመራ እንደመሆኑ መጠን እስከ አሁን በዘርፉ የከፋ ችግር እንዳላጋጠመ አቶ ፍሰኃ ገልጻዋል፡፡

ይህንንም ተሳታፊዎቹ ያረጋገጡ ሲሆን በቀጣይ በሳይት መረጣ ላይ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተካሂዶና በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ቢሆን፣በቁጥጥር ስራ  ባለሙያዎች ከመቆጣጠር ይልቅ በአብዛኛው የመደገፍ አዝማሚያ ቢኖር፣ከቴክኖሎጂ አንጻር ጊዜን፣ጉልበትንና ገንዘብን በመቆጠቡ ረገድ ከፍተኛ ሚና ያላቸውን መጠቀም የሚሉት በአስተያየት ቀርበዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር በአጠቃላይ ኩባንያው ከተቋቋመ አጭር ጊዜ አንጻር  በሁሉም ዘርፍ ይበል የሚያሰኝ ስራን በማከናወን ላይ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ በቀጣይም ይህን እንዲያስቀጥል አሳስበዋል፡፡

በውይይቱ ገንቢ ሃሳቦች ተገኝተዋል ያሉት አቶ ሽመልስ በቀጣይም ሌሎቹም የኢንዶውመንቱ ኩባንያዎች መሰል መድረኮችን እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል፡፡

17/03/2011

ጋፋት ኢንዶውመንት የኢንዶውመንቱን እ.ኤ.አ የ2018 በጀት አመት ያለፉት አስር ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ፡፡

በግምገማው የማስፈጸም አቅም ግንባታ፣ ኢንቨስትመንትን  ማጠናከርና ማስፋፋት ፣ ማህበራዊ ልማት እና የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት የሚሉት አራቱ የኢንዶውመንቱ የትኩረት መስኮች የአስር ወራት አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግመዋል፡፡

በዚህም የማስፈጸም አቅምን ከማጎልበት አንጻር የሰው ኃይሉን በአመለካከትና በክህሎት ለመገንባት የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ማዕከል ያደረጉ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎች መሰጠታቸውና ይህን ተከትሎ የመጡ ለውጦች በጥንካሬ የተነሱ ሲሆን አሁንም የሰው ኃይሉ የወቅቱ  ፉክክር የበዛበትን የቢዝነስ አለም በሚጠይቀው ልክ አለመገኘቱ በእጥረት ተነስቷል፡፡

ኢንቨስትመንትን ከማጠናከር አንጻር በበጀት አመቱ በሁለት መልኩ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማከናወን ታቅዶ ነበር፡፡እነዚህም አዲስ የሚከናወኑ እና የማስፋፊያ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ከዚህ አንጻር ባለፉት አስር ወራት አዲስ የሚቋቋመውን፣ከበቆሎ ስታርችና ተዛማች ውጤቶችን የሚያመርተው እና ከ100 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን  ተጠቃሚ የሚያደርገውን ባህር ዳር የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብርካን ለማቋቋም የገንዘብና መሰል የቴክኖሎጂ አማካሪ የማፈላለጉ ስራ በትኩረት መሰራቱ በጥንካሬ የሚጠቀስ ቢሆንም  አሁንም ቢሆን ፋብሪካውን እውን ለማድረግ በአስር ወራቱ ለማከናወን ከታቀደው አንጻር አፈጻጸሙ እጥረቶች ይስተዋሉበታል ተብሏል፡፡

ከማስፋፊያ ኢንቨስትመንቶች አንጻር የኢንዶውመንቱን የኮንስትራክሽን ኩባንያዎችን በማሽነሪና በቁሳቁስ በማጠናከርና ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ  በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ባለፉት አስር ወራት የተደረጉ ጥረቶች አበረታች ቢሆኑም በዚያው ልክ እጥረቶችም ተስተውለዋል፡፡በጣና ፍሎራ  የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት በዘመናዊ መንገድ ለማስጀመር የጠብታ መስኖ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ ማድረግ ሌላው በበጀት አመቱ ለማከናወን የታቀደ ተግባር ሲሆን  ባለፉት አስር ወራት በተከናወኑ ተግባራት የመስኖ ግንባታው መጀመሩ ሌላው በዘርፉ በጥንካሬ የተጠቀሰ አፈጻጸም ነው፡፡

ከማህበራዊ ልማት አንጻር በበጀት አመቱ ከ አምስት ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት ለ 200 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን ባለፉት አስር ወራት በተከናወኑ ተግባራት ፕሮጀክቱ   በሚከናወንበት እብናት ወረዳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፕሮጀክቱ በይፋ መጀመሩ በጥንካሬ የተጠቀሰ ሲሆን ስራውን በፍጥነት ማስኬድ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በግምገማ መድረኩ ተገልጿል፡፡

የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት ሌላው በመድረኩ የተገመገመ የኢንዶውመንቱ የትኩረት መስክ ሲሆን በዘርፉ ባለፉት አስር ወራት  አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ለማከናወን ከታቀደው አንጻር እጥረቶች የሚስተዋሉበት ነው ተብሏል፡፡

በአጠቃላይ እንዶውመንቱ በበጀት አመቱ ለማከናወን ካቀዳቸው ተግባራት አንጻር  ያለፉት አስር ወራት አፈጻጸም አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት ሲሆን እጥረቶችም ተስተውለዋል፡፡በመሆኑም በበጀት አመቱ ቀሪ አንድ ወር ያልተከናወኑ ተግባራትን ለቅሞ በትኩረት መፈጸም ብሎም አገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታዎችን እየቃኙ ማቀድና መስራት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

21/02/2011

የጋፋት ኢንዶውመንት ኩባንያ የሆነው ጢስ እሳት ውኃ ስራዎች ዘርፉ የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልቶ በመገኘቱ በውሃ ስራዎች ዘርፍ ወደ ደረጃ አንድ አደገ፡፡
ኩባንያው ከዚህ ቀደምም በጉድጓድ ቁፋሮ የስራ ዘርፍ በደረጃ አንድ ደረጃ ስራዎችን ሲያከናውን የነበረና አሁንም በማከናወን ላይ የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን የሚከተሉትን የስራ ዘርፎች ማለትም፡-

  •  የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣የመጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታ፣
  •  የመስኖ አውታሮች ግንባታ፣
  •  የውሃ መጠን ፍተሻ፣
  • የጉድጓድ ጠረጋ፣
  • የእጅ ፓንፕ ተከላና የአናት ግንባታ፣

ስራዎችን በጥራት በመስራት የደንበኞቹን እርካታ ለማረጋገጥ አልሞ በመስራት ይህንንም በተግባር ማረጋገጥ የቻለ ኩባንያ ነው፡፡

14/12/2010 E.C
የጋፋት ኢንዶውመንት ስራ አመራር ቦርድ በ11/12/2010 ዓ.ም ስብሰባ አካሄደ፡፡በስብሰባው የሚከተሉት ዋና ዋና አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡እነዚህም፡-

 • 1ኛ.የስራ አመራር ቦርዱን ሰብሳቢ መሾም
 • 2ኛ.የውጪ ኦዲተር ሪፖርትን ማድመጥ
 • 3ኛ.የኢንዶውመንቱን የስድስት ወር አፈጻጻም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
 • 4ኛ.በአዳዲስ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ

የሚሉት ሲሆኑ በዚህም በተካሄደ ውይይት ዶ/ር ተሾመ ዋለ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል፡፡ከውጪ ኦዲት ሪፖርት አንጻር በቀረበው ሪፖርት ላይ አንዳንድ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰቶባቸዋል፡፡በሪፖርቱም ምንም አይነት የኦዲት ችግር እንደሌለ ተገልጻል፡፡የኢንዶውመንቱና ኩባንያዎቹ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸምን አስመልክቶ በቀረበው የስድስት ወር ሪፖርት ላይም ቦርዱ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡ኢንቨስትመንትን ከማስፋፋት አንጻር አማራጮች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

   

Visitors Counter  

145347
All days
145347

2022-09-27 21:17
   

Facebook Like  

   
   
   
© Gafat Endowment